About US

Melkam-Lib Short-Term Training Center is a locally rooted institution dedicated to advancing the healthcare workforce by preparing individuals to become skilled nursing assistants. We actively collaborate with nursing homes, elderly care centers, homecare providers, and individuals in need of professional caregiving—whether at home or in inpatient settings.

Our core mission is to train and promote highly qualified caregivers who are committed to delivering compassionate, high-quality care.

At Melkam-Lib Caregiver Training Center, we provide comprehensive, hands-on training for those aspiring to support the sick and elderly. Our goal is to build a strong, capable community of professional caregivers ready to meet the growing demands of the healthcare field.

We are dedicated to providing exceptional, compassionate care for the elderly and individuals in need throughout Ethiopia. Our professionally trained caregivers offer personalized support that respects each person’s unique needs, promoting comfort, dignity, and overall well-being.

 

 

መልካም ልብ የአጭር ጊዜ ማሰልጠኛ ማእከል  ለወጣቶች የነርሲንግ ረዳት ስልጠናን በመስጠት የጤና አጠባበቅ የሰው ኃይልን ለማዘመን የሚሰራ ተቋም ነው። ከአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከላት፣ለቤት ውስጥ እና በግላቸዉ ሙያዊ እንክብካቤ ለሚፈልጉ ግለሰቦች በእንክብካቤ ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ከሚያስቀጥሩ ድርጅቶች ጋር በትብብር እንሰራለን።

የእኛ ዋና ተልእኮ ሩህሩህ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንክብካቤን ለማቅረብ ቁርጠኛ የሆኑ ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ተንከባካቢዎችን ማሰልጠን እና ማስተዋወቅ ነው። በተቋማችን ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ጥራት ያለው የእንክብካቤ አገልግሎትን ለመስጠት ብቁ የሆኑ ባለሞያዎችን ማፍራት ነው። ለዚህም ተቋማችን ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሰልጣኞች በስራ ላይ ሲሰማሩ ለሚያገለግሉት ተገልጋይ ፍፁም በሆነ አክብሮት እና ትህትና አንዲሁም ከልብ በመነጨ ፍቅር አገልግሎት እንዲሰጡ የስነምግባር ትምህርት እንሰጣለን ። 

በተግባር ትምህርት የተደገፈውን  ስልጠና የወሰዱ ተንከባካቢዎች የእያንዳንዱን ሰው ልዩ ፍላጎት የሚያከብር፣ ምቾትን፣ እና ደህንነትን የጠበቀ ድጋፍ ይሰጣሉ።

ግባችን እያደገ የመጣውን የእንክብካቤ መስክ ፍላጎቶች ለማሟላት ዝግጁ የሆኑ እና ሙያዊ ብቃት ያላቸው የእንክብካቤ አገልግሎት ባለሞያዎችን በብቃት ማሰልጠን ነው::